አንኳሮች
- የደን ውስጥ ተጓዦች በየዕለቱ ይጠፋሉ፤ ሆኖም ብልህ ዕቅድ ሕይወትዎን ሊታደግ ይችላል
- ከጠፉ ምንም ዓይነት ውሳኔዎች ላይ ከመድረስዎ በፊት ቁጭ ይበሉና ራስዎን ያረጋጉ
- ደን ውስጥ የእጅ ተንቀሳቃሽ ስልክ የኝኙነት መስመር አስተማማኝ አይደለም፤ ይሁንና የአደጋ ጊዜ ምልክት መስጫዎችን መከራየት ይቻላል
- የክፍለ አገር ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት የደን ውስጥ ፍለጋና ትድኛ በጎ ፈቃደኞች በአስቸኳይ አደጋ ወቅት እገዛ ያደርግሉዎታል
95 ፐርሰንት ያህል ሰዎች በጠፉ በ12 ሰዓታት ውስጥ ተፈልገው ይገኛሉ።
ይህም የሚሆነው እንደ ካሮ ራያን የኒው ሳውዝ ዌይልስ ከፍለ አገር ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ባሉ በጎ ፈቃደኞች አይታክቴነት ነው። ወ/ሮ ራያን የደን ውስጥ ጉዞን አስመልክቶ በሙሉ ስሜት የተመሉ የደን ውስጥ ጉዞ መሰናዶ ትምህርት ሰጪ ናቸው።
“ማስታወስ እንዲቻልዎትም ምሕፃረ ቃል አለ። እሱም ይያድይ፣ ይ-ያ-ድ-ይ” ነው።
ይ የቆመው የሚያስፈልግዎትን ይያዙ
ያ የቆመው ሊከውኑ ያሰቧቸው ያስመዝግቡ
ድ የቆመው ድንገተኛ አደጋ ተግባቦቶች ወይም የድንገተኛ አደጋ ምልክት መስጫ
ይ የቆመው የጉዞ መስመርዎን ይወቁ እና ሳይስቱ ይከትሉ
![Bushwalker with map_pixdeluxe Getty.jpg](https://images.sbs.com.au/68/cb/f274c1e94065b02c858c71278254/bushwalker-with-map-pixdeluxe-getty.jpg?imwidth=1280)
Preparedness will increase the likelihood of being found. Credit: pixdeluxe/Getty Images
የሚያስፈልግዎትን ይያዙ
በአነስተኛ የጀርባ ቦርሳ ሊይዟቸው የሚገቡ ነገሮች፤
- እንደ ለውዝ እና ቾኮሌትን ያካታተ ምግብ
- ውኃ – ለየሶስት ሰዓታት አንድ ሊትር
- ጠርዙ ብሩህ ቀለሞች ያሉት ልብስ
- ባርኔጣና የፀሐይ መከላከያ ቅባት
- ለአዋኪ መሬት ጉዞ የሚሆኑ ለእርምጃ ወይም ለሩጫ የተሠሩ ምቹ ጫዎች
- የዝናብ መከላከያ ልብስ
- እንደምን መጠቀም እንዳለብዎት ካወቁ ካርታና ኮምፓስ ወይም የእጅ ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ላይ ኧፕ ይጫኑ
- የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና አሟልቶ የያዘ ቦርሳ
ወ/ሮ ራያን “እንዲሁም አብርዎት ሊሆኑ የሚገቡ ምርጥ ነገሮች ቢኖር የተወሰኑ ጓደኞችዎን ይሆናል” ይላሉ።
ለብቻ መጓዝ የአደጋ ተጋላጭነትን ይጨምራል፤ አብረዎት ሰዎች ካሉ ግና የሚደርስልዎ አለዎት።ካሮ ራይን፣ የኒው ሳውዝ ከፍለ አገር ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ምክትል የቡድን አዛዥ
በጉዞ ወቅት አንድ ቡድን አራት ሰዎች ቢኖሩት ተመራጭ ነው። በዚያ መንገድ አንድ ሰው ቢቆስል፤ ሁለቱ የእርዳታ ጥሪ ሲያደርጉ፤ አንደኛው ከቆሰለው ሰው ጋር መቆየት ይችላል።
![Asian Couple Exploring the Map](https://images.sbs.com.au/89/05/17bf8d244f72b884fa86dd492ffe/gettyimages-611067426-visualspace-couple-exploring-the-map.jpg?imwidth=1280)
It's also vital to let other people know your plans. Credit: visualspace/Getty Images
ሊከውኑ ያሰቧቸውን ያስመዝግቡ
ለብሔራዊ ፓርኮችና የዱር እንሰሳት አገልግሎት፣ ለፖሊስ ወይም ለታማኝ ጓደኛዎ ሊነግሩ ይችላሉ።
በሚናገሩበትም ወቅት የጉዞዎንና የመመለሻዎን መስመሮች በዝርዝር ይግለጡ። ሲመለሱም ቀድመው መሔድዎን ለነገሯቸው መመለስዎንም መንገር እንዳለብዎት አይዘንጉ።
የድንገትኛ አደጋ ምልክት መስጫዎች
የእጅ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ግልጋሎት በደናማ አካባቢ አስተማማኝ አይደሉም። እናም፤ የደን ውስጥ ተጓዦች የግለሰብ ጠቋሚ የአደጋ ምልክት መስጫዎችን መያዝን ሊዘነጉ አይገባም። ይህም ሳተላይቶች ያሉበትን ቦታ ለመጠቆም እንዲችሉ ያግዛቸዋል።
ክሪስቲን ሜየር፤ የደን ጉዞ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ “ለብርቱ ችግር ከተዳረጉ የግለሰብ ጠቋሚ የአደጋ ጊዜ ምልክት መስጫዎን ሊጠቀሙበት ይችላሉ” ይላሉ።
ፖሊስ አስፈላጊ በሆነው መንገድ ሁሉ፤ በሂሊኮፕተርም ይሁን በደን አሰሳ ፈልጎ ሊያገኝዎት ይችላል።ክሪስቲን ሜየር፤ የደን ጉዞ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
የግለሰብ ጠቋሚ የአደጋ ጊዜ ምልክት መስጫን ከውጭ እንቃስቃሴ ሱቆችና ብሔራዊ ፓርኮች፤ ሌላው ቀርቶ በብሔራዊ ፓርኮች አቅራቢያዎ ካሉ ፖሊስ ጣቢያዎች መከራየት ይችላሉ።
እንዲሁም በነፃ የሚጫን አለ። የስልክ አገልግሎትን ይሻል፤ ይሁንና አካባቢዎን ይጠቁምዎታል ለእርዳታ ጥሪ እንዲያደርጉም ያስችልዎታል።
የጉዞ መስመርዎን ይወቁ፤ ወዲያ ወዲህ ሳይሉ ይከተሉ
ወ/ሮ ራያን “ይህም ማለት ወዴት እንደሚሔዱ በትክክል ማወቅ፣ ምልክቶችን መከተል፣ ካርታዎችን መጠቀም፣ በስንት ሰዓት እንደሚወጡ በማወቅ ግማሽ መንገድ ደርሰው መስመርዎን አለመለወጥ ማለት ነው"
“ያስታውሱ፤ ወዴት እንደሚሔዱ የነገሩት ሰው አለ። እናም የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ሰጪዎች የት እንዳሉ ስለሚያውቁ ፈልገው ሊያገኝዎት ይችላሉ" ይላሉ።
ብልህ ይሁኑ፤ የሚስማማዎን የደን ውስጥ ጉዞ ይምረጡ።ካሮ ራያን፤ የኔው ሳውዝ ዌይልስ ከፍለ እር የድንገተኛ አገልግሎት የደን አሰሳና ትድግና ቡድን አዛዥ
አንዱ ሰዎች የሚፈጹሙት የተዘወተረ ስህተት አግባብነት በሌለው የጉዞ መስመርን መመረጥ ነው።
“የእግር ጉዞ ጥንካሬ የተለየ ነው። በተለይም ጀርባችን ላይ አነስተኛ ሻንጣ ተሸክመን በርካታ ደረጃማና ገደላማ መሬት ሲገጥመን። በሞቃት አየር ደግሞ የባሰውን አዋኪ ነው።" ያሉት ወ/ሮ ራያን ጥንካሬያችንን በአግባቡ አለማወቅ የተለመደ ነውም ይላሉ።
![SES Bush Search and Rescue, Blue Mountains_Nicole Bordes.jpg](https://images.sbs.com.au/c1/d2/ed05ab374855af21037648415672/ses-bush-search-and-rescue-blue-mountains-nicole-bordes.jpg?imwidth=1280)
If you don’t have an emergency beacon, try your best to make yourself visible. Credit: Nicole Bordes
ከጠፉ ምን ያደርጋሉ?
በቀዳሚነት የሚፈጽሙት ነገር ቢኖር ቁጭ ብለው እራስዎን ማረጋጋት ነው።
ውኃ ይጠጡ። የካምፕ ማንደጃ ይዘው ያለ ከሆነም ሻይ እንዲያፈሉ በማለት ወ/ሮ ራይን ይመክራሉ።
አክለውም “ቁጭ ማለት ከሰከነ ውሳኔዎች ላይ እንዲደርሱ ያግዝዎታል።”
“ያለማቋረጥ ማሰብ ከቶውንም ለባሰ መጥፎ ድርጊት ይዳርግዎታል። ‘እርግጠኛ ነኝ እዚህ ጥግ አካባቢ ነው’ ይህንን ነው ‘ካርታን ማጉበጥ' የምንለው ብለዋል።
ባለፈው ለመጨመረሻ ጊዜ የነበሩበትን ሥፍራ ያስታውሳሉ? ምናልባትም ምልክት ወይም መጋጣሚያ መንገድን ተመልክተው ይሆናል።
ለአጭር ርቀት ወደ ኋላዎ መራመድ ከቻሉ፤ መንገድዎ ላይ የጭረት ምልክቶችን በእጅዎ ባሉ ነገሮች ያስፍሩ።
ብርቱ ችግር ገጥሞት ያለ ከሆነ፤ እራስዎን ለእይታ ያብቁ። የአየር ጠባዩና ሁኔታዎቹ የሚፈቅድልዎ ከሆነ። የክፍለ አገር ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት እርስዎን ፈልገው ለማግኘት ሂሊኮፕተሮችን ያሠማራልና።
![SES volunteers_Raoul Wegat Getty .jpg](https://images.sbs.com.au/08/e4/d1f282c1441f854dffb45b26f941/ses-volunteers-raoul-wegat-getty.jpg?imwidth=1280)
Around 95 per cent are found within 12 hours by SES Bush Search and Rescue. Credit: Raoul Wegat/Getty Images
ከቆሰሉ ወይም የአየር ንብረቱ መጥፎ ከሆነ መጠለያ ያለበትን ሥፍራ ይፈልጉ። የረጠቡ ልብሶችን ያውልቁ፤ ከቻሉ እሳት ያንድዱ። እንዲያ ማድረጉ የመታየት መጠንንዎን ይጨምራል።
የያዙትን ምግብና መጠጥ አውጥተው ይለዩ። ፈላጊዎችዎን እየጠበቁ ሳለ ውሃና መጠጥዎን መጥነው መጠቀም ያስፈልግዎትልና።
ወደ ደን ውስጥ ጉዞ ከማምራትዎ በፊት
እራስዎንና በዙሪያዎ ያሉ ሰዎችን መርዳት እንዲችሉ፤ የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና ኮርስን ያጠናቅቁ።
የደን ውስጥ ጉዞ ክለብ አባልም ይሁኑ በማለት ክሪስትን ማየር ይመክራሉ።
አያይዘውም “ደን ውስጥ ደህንነትዎ የተጠበቀ እንዲሆን የአንድ ቡድን መጠን ይኑርዎታል። በቀላሉ ተግባቢ የሆኑ ሰዎች ካርታንና ኮምፓስን ማንበብ፣ እንደምን የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ መጠቀም እንደሚችሉና ችግር ሲገጥምዎ ምን ማድረግ እነሚገባዎ ያስተምርዎታል። ይህም ብቻ አይደለም፤ ብዙ ሰዎች የማይሔዱባቸውን እጅግ አስደናቂ የሆኑ ሥፍራዎችን ወስደው ያሳዩዎታል።”
![Bushwalking group_andresr Getty.jpg](https://images.sbs.com.au/fd/f9/d38a919741d9892858d3e3c932fa/bushwalking-group-andresr-getty.jpg?imwidth=1280)
Joining a bushwalking group is a great idea to explore Australia's nature. Credit: andresr/Getty Images
ምንጮች
- በመላ አውስትራሊያ ስላሉ የደን ውስጥ ጉዞ ክለቦችና የደህንነት መረጃ ለማግኘት ይጎብኙ።
- የደን ውስጥ ጉዞ ዕቅድዎን ለ ሊያስመዘግቡ ይችላሉ።
- የካሮ ራያን መምሪያዎች
- የካሮ ራያን – የቀን እግር ጉዞ