የአውስትራሊያ ጦርነቶች ምን ነበሩ፤ ታሪክ ዕውቅና ያልቸራቸው ስለምን ነው?

AusWars_16x9.jpg

The Australian Wars documentary Credit: Blackfella Films

የሠፋሪና ነባር ዜጎች ጦርነቶች ቃሉ በእንግሊዝ የአውስትራሊያ ሠፈራ ወቅት ከ100 ዓመታት በላይ በቅኝ ገዢ ሠፋሪዎችና በነባር ዜጎች መካከል የተካሔዱ ግጭቶችን ለመግለጥ ተዘውትሮ ይነገራል። ምንም እንኳ አውስትራሊያ የተሳተፈችባቸውን የባሕር ማዶ ጦርነቶች ክብር ብትቸርም፤ አሁን ያለችውን ሀገር ለፈጠረው ትግል ግና እስካሁን ዕውቅናን አልቸረችም።


አንኳሮች
  • የአውስትራሊያ ጦርነቶች ዕውቅና የሚቸራቸው "የማንም ያልሆነ ምድር" አዋጅ በሕጋዊ መንገድ ተሞግቶ ሲሻር ብቻ ነው።
  • የአውስትራሊያ ጦርነቶች በመላ አኅጉሪቱ ከመጀመሪያው የ1788 መርከብ አንስቶ እስከ 1930ዎቹ አጋማሽ ያረፉት መርከቦች ድረስ ተካሂደዋል።
  • የቅኝ ግዛት ሬኮርዶችና የአርኪዮሎጂያዊ መረጃዎች በጠበብት የግጭቱ አስከፊ ደረጃ ተገልጧል።
የይዘት ማስጠንቀቂያ፤ የእዚህ መጣጥፍ እና ፖድካስት ማጣቀሻዎች የተወሰኑ ሰዎች ላይ የጭንቀት መንፈስን ሊያሳድር ይችላል።

የባሕር ዳርቻ አውስትራሊያ በመባል የምትታወቀዋ ናት፤ ይህችን መጠነ ሰፊ ምድር 'ባለቤት አልባ ምድር' ሲል ጠርቷታል። ይሁንና የደሴት አኅጉርዋ በመቶዎች የሚቆጠሩ አቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ብሔሮችና ጎሣዎች፣ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነባር ዜጎች ፍጥነት በተመላበት ሁኔታ የእንግሊዝ ዘውድ ‘ቋሚ ተገዢዎች’ ሆነዋል።

ይህም ለ መቀሰቀስ አስባብ ሆነ። በነባር ዜጎችና ሠፋሪዎች መካከል የተካሔዱት ጭካኔ የተመላባቸው ግጭቶችም ለአውስትራሊያ መመሥረት መሠረት ጣሉ። ታሪኩ አሁን ግንዛቤን ማግኘት በመጀመር ላይ ነው።
አውሮፓዊ ደም ያላቸው የአረርንት እና ካልካዶንዋ ሴት ናቸው። "የአውስትራሊያ ጦርነቶች" የተሰኘ ነባር ዜጎች መሬታቸውን ከእንግሊዝ ነጠቃ ለመከላከል ያካሔዱትን የትግል ባሕሪይ በዝርዝር ያካተተ ተከታታይነት ያለው ዘጋቢ ፊልም ሠርተዋል።
እኒህ አውስትራሊያ ውስጥ የተፋለምንባቸው ጦርነቶች ነበሩ፤ ዘመናዊ የአውስትራሊያን ግዛትን የመሠረቱ ጦርነቶች።
ራቼል ፐርኪንስ፤ ፊልም ቀራጭ
በመላ አኅጉሪቷ የተካሔዱት በ1788 ካረፈችው ከመጀመሪያዋ መርከብ ማረፍ አንስቶ እስከ 1930ዎቹ አጋማሽ ድረስ ሲሆን፤ ይሁንና እኒያ ግጭቶች ትምህርት ቤት ውስጥ በትምህርትነት አልተሰጡም ወይም ሌላው ቀርቶ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ዕውቅና አልተቸራቸውም።

አውስትራሊያ ውስጥ በጣሙን ከተከበሩ የጦርነት ታሪክ ተጠባቢዎች አንዱ ናቸው። በ1966 ታሪክ ማስተማር በጀመሩበት ወቅት፤ ነባር ዜጎችን አስመልክቶ አንዳችም ለማገናዘቢነት የሚውሉ ተጠቃሽ የታሪክ መፃሕፍት አልነበሩም።

አለ የተባለውም “ነባር ዜጎችን ያነሳ የነበረው ሁለቴ ብቻ ሲሆን፤ በአለፍ ገደም እንጂ ማውጫ ዝርዝር ላይ እንኳ ሠፍሮ አይገኝም” ብለዋል።

የአውስትራሊያ ጦርነቶች የፊልም ቅንጭብን ይመልከቱ፤
ፕሮፌሰር ሬይኖልድስ፤ ይህ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ እንደ ሙሉ ጦርነት ሳይነገር የቀረው በከፊል በግንባር ጦርነቶች ሳቢያ ነው፤ ግጭቱ ከሽምቅ ውጊያ ጋር ተዝማጅነት ስላለው።

“ምልከታው አንስተኛና የተበታተነ በመሆኑ የጦርነት ሚዛን የሚደፋ አድርጎ ለመወሰድ የማይሆን ነው የሚል ነበር። መደበኛ የመለዮ ለባሽ ልብስ የላቸውም፤ ሠልፈኛ ወታደሮች የላቸውም… ጉዳዮ በተለምዷዊ መልኩ ከቶውንም ግዙፍ መዋቅሮችና ውጊያዎች የሚባሉ አልነበሩም፤ ይሁን እንጂ ግልፅ በሆነ ሁኔታ የጦርነት ይዘት ነበራቸው” ይላሉ።

ሌላው የአውስትራሊያ ግንባር ጦርነቶች በዕሳቤው ይስማማሉ። ይህ ዝንፍ ዕሳቤ የጦርነቶች ግንዛቤ ያስከተላቸው የአንደኛው እና ሁለተኛው ጦርነት ውጤት ነው ባይ ናቸው።

ይሁንና፤ በሰው ልጆች ታሪክ የእዚህ ዓይነት መጠነ ሰፊ ጦርነቶች የተለመዱ አይደሉም።

ዶ/ር ክሌመንትስ “ያኔ ጦርነት እንደሆነ ያውቃሉ። ሁሉም የቅኝ ግዛት ሰነዶች የሚያመለከቱት በጦርነት መልኩ ነው፤ ሆኖም በ20ኛውና 21ኛው ክፍለ ዘመን ያን ዕይታ አጣን። እንዲሁም፤ በርካታ ሰዎች ስለምን እንደ ጦርነት የማይገልጡባቸው ፖለቲካዊ ምክንያቶች አሉ ብዬ አስባለሁ” ብለዋል።

የእኒህ ፖለቲካዊ ምክንያቶች መነሾ የኋልዮሽ ሔዶ በ 'ባለቤት አልባ ምድር' አዋጅና የእንግሊዝ ሕግ መካከል ያለ መጣረስ ነው። ነባር ዜጎች የዘውዱ ዜግነት አልባ ተገዢዎች ተደረገው ተወስደዋል፤ የእንግሊዝ ኤምፓየር ደግሞ "በይፋ ጦርነት ማወጅ... ያን ማድረግ ማለት ጦርነትን በራሳቸው ዜጎች ላይ ማወጅ ተደርጎ ይወሰዳል” በማለት ራቼል ፐርኪንስ ተናግረዋል።

“ሆኖም፤ እንግሊዝ አኅጉሪቷን በቁጥጥራቸው ስር ማድረጉ ሳንካ እንዳይገጥመው ወታደራዊ ኃይልን ተጠቅማለች” ሲሉም አክለዋል።
Frontier War
Frontier conflicts took place across the nation. Source: Supplied / Australian War Memorial Source: Supplied

ማቦ እና የ 'ባለቤት አልባ ምድር' ውድቅ መሆን

የአውስትራሊያ ጦርነቶች ዕውቅናን ማግኘት የሚችለው የ 'ባለቤት አልባ ምድር' እወጃ ሕጋዊ ሙግት ሲገጥመውና ውድቅ ሲሆን ብቻ ነበር፤ በ1990ዎቹ መጀመሪያ የማቦ ውሳኔ በመባል የሚታወቀው ሁነኛ ክስተት እስከገጠመው ድረስ።

“እስካሁን ድረስ የነበረው አመለካከት ነባር ዜጎች የመሬት ባለቤት አይደሉም የሚል ነበር፤ ያም በመሆኑ ሙግቱ ስለ መሬት ባለቤትነት አልነበረም። ስለምን፤ አንዳችም የመሬት ባለቤትነት ሕጋዊ ማረጋገጫ አልባ በመሆናቸው። ከ1992 እና ከዚያ ብይን በኋላ ግና የጦርነቱ ባሕሪይ የግድ መለወጥ ነበረበት፤ ስለምን ጦርነት ሁሌም እንዲህ ካሉ የግዛት ባለቤትነት ጉዳዮች ጋር ተያያዥ በመሆኑ” ሲሉ ፕሮፌሰር ሬይኖልድስ አስረድተዋል።

ዶ/ር ክሌመንስ በፊናቸው የእንግሊዝ ኤምፓየር የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች የአውስትራሊያ መሬት ባለቤትነትን ዕውቅና ለመቸር አመፍቀዱ ያልተለመደ ታሪካዊ ሁነት እንደሆነ ሲናገሩ፤

“ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ማዕከል የአውስትራሊያ ሁኔታ በስህተት የተመላ ነው።እንግሊዝ ቅኝ ከገዛቻቸው ሌሎች አገራት በተለየ፤ እዚህ አውስትራሊያ ውስጥ ለነባር ዜጎች ሉዓላዊነት ዕውቅናን አልቸረችም። ስለምን፤ ከአካባቢው ሰዎች ጋር የቃል ኪዳን ውል የለም፤ የተደረገ የድርድር ጥረት ባለመኖሩ እስካሁኗ ቀን ድረስ ከሕጋዊነት አኳያ የመሬት መብቶቻቸው ምን እንደሁ ለመረዳት ግር ተሰኝተናል” ብለዋል።

እናም ያ ድርድር ያለማካሔድ ክሽፈት ጭካኔ ወደ ተመላበት ደም መፋሰሰ መርቷል።

በጠበብት ቡድኖች የተገኙት የቅኝ ግዛት ሰነዶችና ሥነ ቅርሳዊ መረጃዎች የግጭቱን አስከፊ መጠን አሳይተዋል።

ብቻ ከ400 በላይ የነባር ዜጎች ጥንታዊ አፅመ አስከሬኖችን በመጋዘኑ አኑሮ ይገኛል፤ በርካታዎቹም በርሸና፣ በመቆራረርጥና በጅምላ ግድያ ሕይወታቸው ማለፉን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ራቼል ፐርኪንስ፤ በሕይወት ባሉት የእነሱ ዝርያዎች ዘንድ ሁሌም እንደሚታወሱ አንስተዋል።
አያሌ ነባር ዜጎች ታሪክን ተጭኖ የሚጓዝ መርከብ ሆነዋል። ቀደምት ነባር ዜጎች በእነሱ ላይ የደረሱ ታሪኮችን ለእኛ፣ ለቤተሰቦቻችን አሸጋግረውልናል። እናም፤ ያደግኩት ኩዊንስላንድ ውስጥ በእኔ ሰዎች ላይ ስለደረሰ ጭፍጨፋ፣ ሴት ቅድመ አያቴ ላይ የደረሰውን አመፅ የተመላው ወሲባዊ ጥቃት በማወቅ ነው።
ራቼል ፐርኪንስ፤ ፊልም ቀራጭ
Rachel Perkins - The Australian Wars
Credit: Dylan River/Blackfella Films

ጥቁር ጦርነት

በአውስትራሊያ ታሪክ ውስጥ በጣሙን ብርቱ የግንባር ግጭት ነበር።

“በጥቁር ጦርነት ወቅት ኮሪያ፣ ማሌዥያ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ቬትናምና በሰላም አስከባሪ ግዳጅ ላይ ተጠቃለው ከሞቱት ታዝማኒያውያን በላይ ተገድለዋል” ሲሉ ራቼል ፐርኪንስ በተከታታዩ የአውስትራሊያ ጦርነቶች ዘጋቢ ፊልማቸው ላይ አንስተዋል።

ዶ/ር ኒኮላስ ክሌመንትስ በበኩላቸው በሁለቱም ወገኖች በኩል የነበረው አመፅ በእጅጉ ብርቱ ነበር፤ ቅኝ ገዢ ባለስልጣናቱና ሠፋሪዎቹ "በጣሙን ፍርሃት" ገብቷቸው እንደነበር ሲያመላክቱ፤

“የነባር ዜጎች ተፋላሚነት አስገራሚ ነበር። አንዱ አንዱን በሚያውቅበት የቅኝ ግዢ ዓለም ውስጥ ማን በነባር ዜጎች እንደተገደለ ወይም እንደቆሰለ፣ ማን እርሻቸውን እንዳጋየ ያውቃሉ። ፍፁም አስፈሪ ነበር” ብለዋል።
እንደ እውነቱ ከሆነ፤ ቆም ብለው የሚያስቡ ሰዎች ቅኚውን ትተው ለመሔድ ያሰላስሉ ነበር።
ዶ/ር ኒኮላስ ክሌመንትስ፤ የአውስትራሊያ ታሪክ ተጠባቢ
ይሁንና አውሮፓውያኑ አሸነፉ፤ የታዝማኒያ ነባር ዜጎችን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ ያህል ደርሰው ነበር።

አመፅ በታከለበት ወሲባዊ ጥቃት ሳቢያም ግጭቱ ተባብሷል።

ዶ/ር ክሌመንትስ “ለአመፁ መቀስቀስ፣ እሳት ለመጫር አስባብ የሆነው አመፅ የተላበሰው ወሲባዊ ጥቃት ነው” በማለትም አክለዋል።

በነባር ሴቶች ላይ ይካሔድ የነበረው የተቀናጀው ወሲባዊ ጥቃትና እገታ በእጅጉ የተለመደ ነበር፤ በተወሰኑ የነባር ዜጎች ጎሣዎች ላይ የደረሱትን ወሲባዊ ጥቃቶችን ተቋቁሞ መቆየትን በተመለከተ ሲናገሩም፤

“ዛሬ ታዝማኒያ ውስጥ የነባር ዜጎች ዝርያዎች ሊኖሩን የቻሉት በመነመነ ሁኔታ ነው፤ በአብዛኛው በአመፅ ሳቢያ፤ ከቶውንም ተሟጥጠው ጠፍተው ነበር” ብለዋል።
What is Native Title explainer NITV Eddie Koiki Mabo
Eddie Mabo with his legal team. Source: SBS Credit: National Museum of Australia

እሳትን በእሳት መፋለም

ቅኝ ገዢዎች የነባር ዜጎች አማፅያንን ከበርካታ የአውስትራሊያ ክፍሎች ለመደምሰስ፤ ሽብርን የሚያሰፍን አገር በቀል ፖሊስና ስልጡን ፓራሚሊሺያ ኃይል አቋቋሙ።

'አገር በቀል ወታደሮችን ትመለምልና እንደ ወታደራዊ ኃይል ትጠቀምባቸዋለህ። ይህ ያለምንም ጥርጥር የነባር ዜጎችን አማፂያን ለመስበር ዋነኛ ኃይል ነበር' ሲሉ ፕሮፌሰር ሬይኖልድስ አመላክተዋል።

ምልምሎቹ የደንብ ልብስ፣ ጠብመንጃዎችና ፈረሶች ተሰጣቸው። ዶ/ር ክሌመንትስ ነባር ዜጎቹ በነጭ መኮንኖች እንደተታለሉና ባሕላዊ የነባር ዜጋ እውቀታቸውንና የጫካ ክህሎታቸውን እንደተጠቀሙበት ያላቸውን እምነት ሲገልጡ፤

“የጉዳቱ ቁጥር በኩዊንስላንድ አገር በቀል ፖሊስ ብቻ የተመለከተው በአሥር ሺህዎች የሚቆጠር ነው። ግምቶች ከ 60 እስከ 80.000 ይደርሳሉ። ፍፁም አስደንጋጭ ነው ብዬ አምናለሁ፤ ጠቅላላው አስቀያሚው ድርጊት የሞራል ግርዶሽ ይጋርዳል” ብለዋል።
Australian Aboriginal camp in the nineteenth century
A nineteenth century engraving of an aboriginal camp - Marmocchi Source: Getty Source: Getty
ራቼል ፐርኪንስ፤ ተከታታዩን የአውስትራሊያ ጦርነቶች ፊልም ታሪክ ሲቀርፁ እኒህን ሁሉ መጋፈጥ ነበረባቸው።

“ቀደም ሲል ሰምቼ የማላውቀውን፤ በሴት አያቴ ስለ እናቷ ቤተሰብ በጅምላ መጨፍጨፍ የተቀረፀውን አደመጥኩ። ሁነቱ የተፈፀመበት ሥፍራ ተገኝቼ አላውቅም። የት እንደተፈፀመም አላውቅም ነበር፤ ተከታታዩን ዘጋቢ ፊልም እስከ ቀረፅኩ ድረስ” በማለት አንስተዋል።

ቀደምት ቤተሰቦቻቸው ከሠፋሪዎቹ ወገን የሆነው ዶ/ር ክሌመንትስ በበኩላቸው፤ ሁሉም አውስትራሊያውያን የሐፍረት ስሜቶችን በመወጣት ያለፉትን ኢ-ፍትሐዊነቶች ገልጠው ሊያሳዩ እንደሚገባ ሲያመላክቱ፤

“የአንድ ሰው ቀደምት ቤተሰቦች ተሳተፉበትም አልተሳተፉበት፤ ሁላችንም የተሰረቀ ነባር ዜጎች መሬት ወራሾች ነን። በትንሹ፤ ይህን ታሪክ የመግለጥ፣ ከታሪኩ ጋር አብረው የሚመጡ ግድ አሰኚ ሁነቶችንም አክሎ ለመፃኢው ጊዜ አዎንታዊ ሚናን መጫወት ይገባል” ሲሉ ልብ ያሰኛሉ።
Nowhere was resistance to white colonisers greater than from Tasmanian Aboriginal people, but within a generation only a few had survived the Black War.
Nowhere was resistance to white colonisers greater than from Tasmanian Aboriginal people, but within a generation only a few had survived the Black War. Source: The Conversation / Robert Dowling/National Gallery of Victoria via The Conversation Source: The Conversation / Robert Dowling/National Gallery of Victoria via The Conversation

ይህ ታሪክ የማይዘከረው ስለምን ነው?

ፕሮፌሰር ሬይኖልድስ፤ የተሰው ወታደሮችን በበርካታ የጦርነት ዝክረ መታሰቢያዎቿ ክብር የምታላብሰዋ ሀገረ አውስትራሊያ፤ በዕንቆቅልሽ በታጀሉ የሰብዓዊ ወንጀል ድርጊቶች ዕውን በሆኑ የግንባር ጦርነቶች ስለ መፈፀማቸው በአደባባይ ዕውቅና ልትቸር እንደሚገባ የሚያምኑ መሆኑን ሲጠቁሙ፤

“እንደምን ሆኖ ነው የአውስትራሊያ ጦርነቶችን መቀበል የተሳነን?” በማለት ይጠይቃሉ።

አክለውም “ይህ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ዕውን የሆነ አይደለም፤ ለሁሉም [ከአገር በቀል አሜሪካውያን] ጋር የነበሯቸውን ግጭቶች በይፋ እንደ ጦርነቶች ዕውቅና ቸረዋል። ግልፅ ነው ኒውዚላንድ ውስጥም እንዲያ ነው፤ የማኦሪ ጦርነቶች ሁሌም በጣሙን ጠቃሚ የታሪክ አካል ሆኖ አለ” ብለዋል።

ራቼል ፐርኪንስ ለእዚህ ያልተለመደ ቀላሉ ምክንያት፤

“አውስትራሊያ በዓለም ቅኝ ገዢዎች ያልለቀቁባት ልዩ ሥፍራዎች አንዷ መሆኗ ነው” ይላሉ።
ገዢዎቹ ወይም ሠፋሪዎቹ ለቅቀው አልሔዱም! ከያኔ ጀምሮ የጨበጡት ስልጣን አሁንም ድረስ አብሯቸው አለ። እናም፤ ሀገራቸውን ላለማስደፈር የቅኝ ገዢዎችን ኃይል ለተፋለሙት ዕውቅና ለመቸር ወይም ለመዘከር ለሀገሪቱ በመጠኑ ከፍ ያለ አዋኪ ሁኔታ ይሆናል።
ራቼል ፐርኪንስ፤ ፊልም ቀራጭ
ዶ/ር ክሌመንትስ፤ ማኅበረሰቡ ለተሰው ወታደሮች መዘከሪያ ‘እኛ አንዘነጋቸውም’ የሚለው ቃለ ሐረግ፤ ሀገራቸውን ከእንግሊዝ ወረራ ለመከላከል የተፋለሙትንም አርበኞች ሊያካትት ይገባል የሚል ዕሳቤያቸውን ሲያጋሩ፤

“ሀገሬ ወኔን ተላብሳ ላለፈ ታሪኳ እውቅናን ብትቸር፣ ቀደምቶች ለፈፀሙት ስህተቶችና ለወደፊቱም በሚቻላት አቅም ሁሉ ስህተቶችን ለማረም ብትቆርጥ በእጅጉ ኩራት ይሰማኝ ነበር… ልጆቼ መዘክሮች ይሁኑ ወይም ከዝንቅ ስሞች ጋር፣ ነባር ዜግነት ባለበት፣ በተከሰተበት፣ ዕውቅና በተቸረበት መልክአ ምድር እንዲሔዱ እሻለሁ” ብለዋል።

በ SBS On Demand በአምስት ቋንቋዎች፤ ቀላል ቻይንኛ, አረብኛ, ልማዳዊ ቻይንኛ, ቬትናምኛ እና በኮሪያ ቋንቋ መምልከት ይቻላል። ተካታትይ ፊልሞቹ ከማብራሪያዎች/ የትርጉም ፅሑፎች ጭምር/ ማየት ወይም በከፊል ማየት ለተሳናችው አድማጮች በኦዲዮ ጭምር ተዘጋጅተው ይገኛሉ።
ይህ ፅሑፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕትመት የበቃው በወርኅ ሴምፕቴምበር 2022 ነው።

Share