"ሕዝብና መንግሥት ከደገፉን ጮቄ ተራራ፣ጉና ተራራና ላሊበላ አቡነ ዮሴፍ እንዲተሳሰሩ ለማድረግ አቅሙና ዕውቀቱ አለን" ዐቢይ ዓለሙ

Tourists.jpg

Tourists. Credit: A.Alem

የሙሉ ኢኮቱሪዝም መሥራች ዐቢይ ዓለም፤ እንደምን የተጋረጡበትን ተግዳሮቶች ተወጥቶ ከጮቄ ማኅበረሰብ አባላት ጋር በጋራ የ2022 'ድንቅ የቱሪዝም መንደር' ተመራጭና ተሸላሚ ለመሆን እንደበቁ ይናገራል። ዳግም የትብብር ጥሪም ያቀርባል። የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ የሚካሔደው በሳዑዲ አረቢያ ከፌብሪዋሪ 27-28, 2023 / የካቲት 20 - 21, 2015 የመጀመሪያው የዓለም ቱሪዝም ድርጅት አውታረ መረብ ድንቅ የቱሪዝም መንደሮች ስብሰባ በሚካሔድባት አሉላ ከተማ ነው።


አንኳሮች
  • የጮቄ ቱሪዝም አስተናጋጆችና ተስተናጋጆች ልዩ መስተጋብር
  • የባሕልና ዕውቀት ልውውጥ
  • የአካባቢ ጥበቃ

Share