Life and Legacy: Fikrou Kidane – Pt 1

Life and Legacy: Fikrou Kidane – Pt 1

Fikrou Kidane Source: Courtesy of FK

ጋዜጠኛ ፍቅሩ ኪዳኔ፤ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኛ ናቸው። ተኮትኩተው ያደጉት በታላቁ የኢትዮጵያ ዘመናዊ ስፖርት መሐንዲስ ይድነቃቸው ተሰማ ነው።


በምልሰት የሕይወት ጎዞ ጅምራቸውንና ዘመን ያጎለመሰ ወርቃማ አሻራቸውን ነቅሰው የሚያወጉት ዕትብታቸው ከተቆረጠበት የአዲስ አበባው ፍልውኃ ሆስፒታልና ቦርቀው ካደጉባት ጉለሌ ሠፈር ነው።
Life and Legacy: Fikrou Kidane – Pt 1
Fikrou Kidane Source: Courtesy of FK
የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ጊዜ የስፖርት ጋዜጠኛ ይሁነኝ ብሎ የቀጠረው ፍቅሩ ኪዳኔን ነው። በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ ውስጥም ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ስታዲየም ኢንተርናሽናል የእግር ኳስ ግጥሚያን በሬዲዮ ያስተላልፉትም እሳቸው ናቸው።
Life and Legacy: Fikrou Kidane – Pt 1
Fikrou Kidane Source: Courtesy of FK
ፍቅሩ ኪዳኔ፤ በአገር ውስጥ የስፖርት ጋዜጠኛነት ተወስነው አልቀሩም፤ ባሕር ማዶ ተሻግረው የስፖርት ዓለም አባታቸውን የይድነቃቸውን ዱካ ተከትለው የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት እስከ መሰየም ደርሰዋል።

ከዘመናችን የዓለም መሪዎች ጋር በስፖርቱ ዘርፍ መክረዋል።
Life and Legacy: Fikrou Kidane – Pt 1
Source: Courtesy of FK
በ፲፮ኛው የሜልበር - አውስትራሊያ የበጋ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ላይ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እ.አ.አ. በ1956 ዓ/ም ስትሳተፍ በኢትዮጵያ አየር ኃይል DC-3 አውሮፕላን ከኢትዮጵያውያን አትሌቶችና የቡድን መሪዎች ጋር ተሳፍረው 125 ሰዓታት በፈጀ በረራ በኦሎምፒክ መንደር ተገኝተዋል። የአገራቸውን የመጀመሪያ የኦሎምፒክ ተሳትፎ ዋቤ ሆነው ዘግበዋል።

የክፍል አንድ ትረካቸው የሚያጠነጥነውም በእኒህ ጉዳዮች ዙሪያ ነው።


Share